በቦሩ በራቃ* ረሃብ ኢትዮጵያ ውስጥ በተሰማ ቁጥር የወሎው ወገናችን ስም ሁሌም ቀድሞ ይነሳል። ከ40 ኣመት በፊት የጀመረው ይህ በገዢዎች ሆን ተብሎ ትኩረት የተነፈገው ፖለቲካ-ወለድ የረሃብ ኣዙሪት ዛሬም ድረስ ቀጥሏል። ያኔ ንጉሱ የ80 ኣመት ልደታቸውን ያከብሩ ነበር። በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከድሃ ኣገር ካዝና አየወጣ እንደ ውሃ ይረጫል። ድግስ ከበርቻቻው በቤተ መንግስቱ ድምቁዋል። ንጉሱና ባለሙዋሎቻቸው በፌሽታ ግለው […]
↧